ኦቶፋጂና ጾም

ኦቶፋጂና ጾም

July 27, 2023

ኦቶፋጂ ምንድን ነው? ኦቶፋጂ ማለት ህዋሶቻችን አላስፈላጊ ህዋሶችንና የህዋስ ክፈሎችን በመመገብ ሀይል የሚያመነጩበትና ሰውነታችን የሚታደስበት ሂደት ነው፡፡

ጥቅሞቹ በሽታ የመከላከል ብቃት ይጨመራል ስኳር ደም ግፊትና ኮለስትሮል ይከላከላል በመርሳት በሽታና በካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል

ኦቶፋጂን ለማነቃቃት ምን እናድርግ?

መጾም፡፡ በጾም ወቅት ሰውነት ሀይል ለማመንጨት የራሱን ህዋስ ወይም የህዋስ ክፍሎች ይበላል፡፡ በዚህ ሂደት ሰውነት እራሱን በራሱ ያጸዳል፡፡ ይህን ውጤት ለማግኝት በብዛት ከሚጠቀሱ የጾም አማራጮች መካከል፡ለ 18 ሰዓታት በተከታታይ መጾምና በቀሪው 6 ሰዓታት ውስጥ መመገብ ወይም ለ 16 ሰዓታት በተከታታይ መጾምና በቀሪው 8 ሰዓታት ውስጥ መመገብ አሊያም በ 24 ሰዓታት ውስጥ አንዴ መመገብ ይጠቀሳሉ

ጥንቃቄ!!

ይህን መንግድ ከመከተሎ በፊት ሀኪሞን ያናግሩ

Related articles

Please select listing to show.